አዲስ አበባ የካቲት 1/2002(ሬዲዮ ፋና) የፌዴራልና የክልል መገናኛ ዘርፍ ተቋማት አምስተኛ የጋራ የምክክር ጉባኤ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል።
የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው መንግስቴ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደገለጡት በየአካባቢው የመሰረተ ልማት አውታሮችን በማስፋፋት የአገልግሎቱን ጥራት ለመጠበቅ የሚካሄደው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።
ባለፉት ዓመታት የመንገድ፣ የስልክ፣ የአየር ትራንስፖርትና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮችን በማስፋፋት ረገድ የተከናወኑት ሥራዎች ስኬታማ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡቦንግ በበኩላቸው መሰረተ ልማት አውታሮች ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል ።